Thursday, 28 November 2013

የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲን እንደገና ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ጸደቀ።

ከፋና ድረ ገፅ


አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ሁለት አዋጆችን አጸደቀ።
ምክር ቤቱ በቅድሚያ ያጸደቀው የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲን እንደገና ለማቋቋም የቀረበውን አዋጅ ነው።

በአዋጁ ኤጀንሲውን ማቋቋም ያስፈለገው በአሁኑ ጊዜ የሃገራችን ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት በቀጣይ ለማረጋገጥ እንዲሁም ሃገሪቱ የተደቀኑባትን ስጋቶች በአስተማማኝ መልኩ ማምከን እንዲቻል ነው ተብሏል ።

የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች ኢንዱስትሪዎች የባቡር ኔትወርክና የአቪየሺን ስራዎች ለጥቃት ተጋላጭ በመሆናቸው ደህንነታቸውን ማረጋገጥ ቀጣይ የኤጀንሲው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑም በአዋጁ ተገልጻል።

 ምክር ቤቱ  የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን አዋጅ ያጸደቀ ሲሆን ፥ ከዚህ በፊት የወጡ አዋጆች በአንድ ተጠቃለው የተለያዩ ሀላፊነቶች እና የነበሩ ክፍተቶች እንዲደፈኑ የሚያስችል ነው።

ከተቋሙ ወቅታዊ ግዳጅ ጋር የሚጣጣም እና ግዳጁን ታሳቢ ያደረገ የህግ ረቂቆችም ታክለወብታል።
ምክር ቤቱ በሁለቱም አዋጆች ላይ በዝርዝር ከመከረ በኋላ አዋጆቹን  አጽድቋል።