መቀመጫውን ኒውዮርክ
ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ‘ሂውማን ራይትስ ዎች’ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የስልክና የኢንተርኔት
ግንኙነቶችን እንደሚሰልል መጋቢት 16 ባወጣው ሪፖርቱ ገለፀ።
የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ
145 ገፅ በሚደርሰውና “THEY KNOW EVERYTHING WE DO: Telecom and InternetSurveillance in Ethiopia” የሚል ርእስ
በሰጠው ሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግስት የቻይናና የአውሮፓ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በኢትዮጵያና በባህር ማዶ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዜጎችን
የስልክና ኢንተርኔት እንቅስቃሴ እንደሚሰለል ገልጿል።
ስለ ሪፖርቱ ኤ.ኤፍ.ፒ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ሚንስተር አቶ ሬድዋን ሁሴን
“የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለማጥፋት ከሚደረጉ ዘመቻዎች አንዱ መሆኑን ስለምናውቅ ለሪፖርቱ መልስ መስጠት አስፈለጊ አይደለም”
በማለት ሪፖርቱን ቢያጣጥሉም ምንጮቻችን እንደገለፁት ከሆነ የመንግስት የስለላ ክንፍ የሆነው የመረጀና ደህንነት ኤጀንሲ INSA
የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ በለቀቀው ሪፖርት ተደናግጠው ‘ውስጣችን መረጃ አሳልፎ የሚሰጥ አለ’ እስከማለት እንደደረሱ ምንጮቻችን ገልፀውልናል።
ሂውማን ራይትስ ዎች በርፖርቱ አያይዞ የደህንነቶች ሀይሎች የተቀዱ የስልክ ልውውጦችን በፈለጉት
ጌዜ የሚያዳምጡ ሲሆን ካለምንም ህጋዊ ድጋፍ የዜጎችን ስልክ ጠልፎ በመቅዳት የተቃውሞ ድምፅን ለማፈን እንደሚጠቀሙበትና በአገር
ውስጥም ከአገር ውጭም የሚገኙ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚዎች ኮምፒተሮች ላይ ለስለላ የሚያገለግል ሶፍትዌር (spyware) በመላክ
በኦንላይን የሚያደርጉትን እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን እንደሚሰልል ርፖርቱ ጠቅሷል።
በኢንተርናሽናል ኮምንኬሽን ዩንየን ጥናት መሰረት 23% ኢትዮጵያውያን የተንቀሳቀሽ ስልክ ተጠቃሚ
ሲሆኑ፣ በስለላው ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያን መንግስት ትደግፋለች ተበላ የምትወቀሰው ቻይና