የዲጂታል ዘመን
መምጣት ይዟቸው ከመጡ
ጠንቆች መካከል የገዛ
ሰላይን ይዞ መዞር
ነው። የዴስክቶፕ እና የላፕቶፕ
ኮምፒዩተሮች፣ ስልኮች እንዲሁም
ታብሌቶች የስለላ መሣሪያ
በመሆን በተለያዩ መንገዶች
መረጃዎቻችንን አሳልፈው የሚሰጡባቸው
መንገዶች አሏቸው። የዚህ
ጽሑፍ ዓላማ ማልዌር በመባል የሚታወቁ
በኮምፒዩተሮቻችን ላይ ተጭነው
የሚሰልሉንን የሶፍትዌር ዓይነቶች
እንዴት ኮምፒዩተሮቻችን ላይ
ከመጫናቸው በፊት
በቀላሉ መከላከል እንደምንችል
ነው።
ማልዌር ምንድን ነው?
ባለፈው ሰሞን
ሲቲዝን ላብ ካወጣቸው
መረጃዎች መካከል፣ የኢትዮጵያ
መንግሥት ሁለት የኢሳት
ጋዜጠኞችን በማልዌር ለመሰለል
የተደረገው ሙከራ ይገኝበታል።
ሙከራው የተደረገው በፒዲኤፍ ፎርማት የተዘጋጁ የሚመስሉ ዶክመንቶችን መረጃ ብለው በመላክ ነገር ግን ማልዌር ሶፍትዌሩ ጋዜጠኞቹ
ኮምፒዩተር ላይ ለመጫንና ለመሰለል ነው፡፡ ሙከራው ቢሳካ ኖሮ ጋዜጠኞቹ በቀላሉ የኢሜይል እና የሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻቸውን
የይለፍ ቃሎች ይሰረቁና የነበራቸው መረጃ ከመበርበሩም በተጨማሪ በነርሱ ስም ሌሎች ሰዎች ጋር በመገናኘት ሰላዮቻቸው ተጨማሪ
መረጃ ሊቆፍሩ ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ አደጋው ለነርሱም፣ ከነርሱ ጋር የኢሜይል ግንኙነት ላላቸውም ሰዎች ጭምር ነው ማለት
ነው፡፡
ይህ በማንኛውም
ጋዜጠኛ፣ አራማጅ ወይም
ተቃዋሚ ዜጋ ላይ
ሊደርስ የሚችል በአምባገነኖች
የሚሰነዘር አደጋ የተለመደ አደጋ ነው።
ከመንግሥታት በተጨማሪም ግለሰቦች ለተለያዩ ግቦች ማልዌሮችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
ማልዌር የሚለው ቃል malicious software ከሚሉት የእንግሊዝኛ
ሁለትቃላት ገሚስ ጥምረት የተፈጠረ ቃል ነው፡፡ ማልዌር ሶፍትዌሮች የኮምፒዩተርን ጤነኛ አገልግሎት ለማዛባት እና መረጃ ሰብስቦ
በኢንተርኔት ግንኙነት ወቅት አሳልፎ ለሌላ አካል ለመላክ የሚረዱ አደገኛ የሶፍትዌር ዓይነቶች ናቸው፡፡ ማልዌሮች
ወደኮምፒዩተሮች በተንቀሳቃሽ ዲስኮች ወይም በኢንተርኔት ግንኙነት ወቅት ሊገቡ ይችላሉ፤ ሆኖም ተጠቃሚው ካልጫናቸው በስተቀር
ራሳቸውን መጫን ስለማይችሉ ገና ከጅምሩ ራስን መጠበቅ ይችላሉ፡፡
የኮምፒዩተሩ ተጠቃሚ ማልዌሩን እንዲጭነው አዘጋጆቹ የተለያዩ
ማታለያዎችን ይጠቀማሉ፡፡ በጣም የተለመዱት ማታለያዎች የተላከውን ፋይል አይከን የኦፊስ ዶክመንቶች አይከን (ዎርድ፣ ኤክሴል፣
ፓወር ፖይንት…)፣ የፒዲኤፍ ዶኩመንት፣ ወይም የሙዚቃ ፋይል አይከን በማድረግ የሚላኩ ናቸው፡፡ ተጠቃሚው እነዚህን ፋይሎች
ለመክፈት በሚያደርገው ሙከራ ማልዌሮቹ ራሳቸውን ኮምፒዩተሩ ላይ ይጭናሉ፡፡ ከዚያ የታቀደላቸውን ጥፋት ኮምፒዩተሩ ላይ
ይፈፅማሉ፡፡
ማልዌሮችን አንቲቫይረሶች የሚለዩዋቸው ቢሆኑም አንቲቫይረሶች የማይለይዋቸው
ማልዌሮችም ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህን ሐሰተኛ ሶፍትዌሮች (ማልዌሮች) አለመክፈት ከሁሉም የተሻለው መፍትሔ ነው፡፡
ማልዌሮችን
እንዴት እናውቃቸዋለን?
ማልዌር ፋይሎች ‹FileName.exe› (ኢ.ኤክስ.ኢ.) ኤክስቴንሽን ያላቸው ስለሆነ እንደዚህ
ዓይነቶችን ፋይሎች በሚገባ ከምናውቀው/ከምናምነው ምንጭ ያገኘነው ሶፍትዌር ካልሆነ በስተቀር አለመጫን ሁነኛው መፍትሄ ነው፡፡
![]() |
ምስል 1. የፋይል
ስሙ የማታይና የሚታይ ፋይል
|
ከላይ ስዕሉ ላይ እንደሚታየው ኤክስቴንሸኑ
የፋይል ስም የሆነው ቢከፈት ምንም አደጋ የሌለው ሲሆን፣ ኢ.ኤክስ.ኢ. የሆነው ግን (በተለይ የሌላ ፋይል አይከን ለምድ ከለበሰ)
ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ኢ.ኤክስ.ኢ. የሆኑ ፋይሎችን ደብልክሊክ ማድረግ ኮምፒዩተሩ ላይ ሶፍትዌሩ እንዲጫን መጋበዝ ነው፡፡
ቀጣዩ ጥያቄ ኮምፒዩተሮቻችን የፋይሎችን
ኤክስቴንሽን የማያሳዩ መሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህ፣ ኮምፒዩተሮቻችን ሁሌም የፋይሎቹን ኤክስቴንሽን እንዲያሳዩ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ይህንን ለማድረግ ማንኛውንም ፎልደር በመክፈት View የሚለው ሜኑ ውስጥ Folders Option የሚለውን በመምረጥ ከታች በሚታየው
ምስል ውስጥ ያለውን ዲያሎግ ቦክስ መጥራት ይቻላል፡፡ ከዚያም ቪው የሚለው ታብ ውስጥ በመግባት በቀይ ቀስት የተመለከተችውን ሳጥን
(hide extensions for known file types) የሚለውን uncheck በማድረግ ሁልጊዜም የፋይሎችን ኤክስቴንሽን
ማድረግ ይቻላል፡፡
![]() |
ምስል 2. የፋይል
ኤክስቴንሽኖች የሚያሳየን ፎልደር ኦፕሽን
|
No comments:
Post a Comment