ምንጭ አድማስ
በኢትዮጵያ የቴሌኮም ፕሮጀክት ላይ ላለፉት 12 ዐመታት ሲሰራ የቆየው ዜድቲኢ አሁን በመካሄድ ላይ ባለው የቴሌኮም ማስፋፊያ ፕሮጀክት 50 በመቶ ድርሻ መውሰድ የሚታወቅ ሲሆን፤ በኤሌክትሪክ ሐይል ሥርጭት፣ በትምህርት አቅርቦትና በከተማ አስተዳደር ዙሪያ ሶስት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋውቋል።
ፓወር ግሪድ፣ ኢ— ለርኒንግና ስማርት ሲቲ በመባል የሚታወቁትእነዚህ ቴክኖሎጂዎች የተሳለጠ የከተማ አኗኗር ለመፍጠር የሚያስችሉና በከተማ አስተዳደር ውስጥ ወሳኝ የሚባሉትን መሰረታዊ መረጃዎች በማጠናከር አመራርን ዘመናዊ ለማድረግ የሚያግዙ ናቸው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ለአገር ውስጥ ገበያ የተዋወቁት የቴክኖሎጂ ውጤቶች በፍጥነት እያደገች ቻይና እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተተግብረው ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገቡ መሆናቸውን ዜድቲኢ ገልጾ፤ በአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አምራችነት ቀዳሚ ሥፍራ ለማግኘት አስችሎኛል ብሏል።
ስማርት ሲቲ የተሰኘው ቴክኖሎጂ የ 2013 የአለም አቀፍ የሞባይል ቴክኖሎጂ የሽልማት አሸናፊ እንደሆነ በቤጂንግ ከተማ ተተግብሮ የአለም አቀፍን የፈጠራ ተሸላሚ ለመሆን እንደበቃ ኩባንያው ገልጿል። ኢለርኒንግና ፓወር ግሪድ የተባሉት ቴክኖሎጂዎችም ከቻይና በተጨማሪ በሞሪሽየስ፣ በቬንዝዌላና በኬንያ ተሞክረው ውጤታማ መሆናቸው ጠነግሯል።
በፍጥነት እያደጉ ባሉት የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ውጤታማ እደሚሆኑ ዜድቲኢ ጠቅሶ፤ የኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት በ2020 ወደ 120 ሚሊየን ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅና ከዚህም ውስጥ 60 በመቶ ያህሉ በከተማ ይኖራል ተብሎ እንደሚገመት ተናግሯል።
No comments:
Post a Comment