Monday, 31 March 2014

ኮምፒውተራችንን ከማልዌር (ሰላይ ሶፍትዌር) መከላከያ ቀላል መንገድ




የዲጂታል ዘመን መምጣት ይዟቸው ከመጡ ጠንቆች መካከል የገዛ ሰላይን ይዞ መዞር ነው። የዴስክቶፕ እና የላፕቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ስልኮች እንዲሁም ታብሌቶች የስለላ መሣሪያ በመሆን በተለያዩ መንገዶች መረጃዎቻችንን አሳልፈው የሚሰጡባቸው መንገዶች አሏቸው። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ማልዌር በመባል የሚታወቁ በኮምፒዩተሮቻችን ላይ ተጭነው የሚሰልሉንን የሶፍትዌር ዓይነቶች እንዴት ኮምፒዩተሮቻችን ላይ ከመጫናቸው በፊት በቀላሉ መከላከል እንደምንችል ነው።

ማልዌር ምንድን ነው?

ባለፈው ሰሞን ሲቲዝን ላብ ካወጣቸው መረጃዎች መካከል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለት የኢሳት ጋዜጠኞችን በማልዌር ለመሰለል የተደረገው ሙከራ ይገኝበታል። ሙከራው የተደረገው በፒዲኤፍ ፎርማት የተዘጋጁ የሚመስሉ ዶክመንቶችን መረጃ ብለው በመላክ ነገር ግን ማልዌር ሶፍትዌሩ ጋዜጠኞቹ ኮምፒዩተር ላይ ለመጫንና ለመሰለል ነው፡፡ ሙከራው ቢሳካ ኖሮ ጋዜጠኞቹ በቀላሉ የኢሜይል እና የሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻቸውን የይለፍ ቃሎች ይሰረቁና የነበራቸው መረጃ ከመበርበሩም በተጨማሪ በነርሱ ስም ሌሎች ሰዎች ጋር በመገናኘት ሰላዮቻቸው ተጨማሪ መረጃ ሊቆፍሩ ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ አደጋው ለነርሱም፣ ከነርሱ ጋር የኢሜይል ግንኙነት ላላቸውም ሰዎች ጭምር ነው ማለት ነው፡፡

ይህ በማንኛውም ጋዜጠኛ፣ አራማጅ ወይም ተቃዋሚ ዜጋ ላይ ሊደርስ የሚችል በአምባገነኖች የሚሰነዘር አደጋ የተለመደ አደጋ ነው። ከመንግሥታት በተጨማሪም ግለሰቦች ለተለያዩ ግቦች ማልዌሮችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

Sunday, 30 March 2014

ZTE አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ሊያቀርብ ነው።

ምንጭ አድማስ

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ፕሮጀክት ላይ ላለፉት 12 ዐመታት ሲሰራ የቆየው ዜድቲኢ አሁን በመካሄድ ላይ ባለው የቴሌኮም ማስፋፊያ ፕሮጀክት 50 በመቶ ድርሻ መውሰድ የሚታወቅ ሲሆን፤ በኤሌክትሪክ ሐይል ሥርጭት፣ በትምህርት አቅርቦትና በከተማ አስተዳደር ዙሪያ ሶስት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋውቋል።

ፓወር ግሪድ፣ ኢ— ለርኒንግና ስማርት ሲቲ በመባል የሚታወቁትእነዚህ ቴክኖሎጂዎች የተሳለጠ የከተማ አኗኗር ለመፍጠር የሚያስችሉና በከተማ አስተዳደር ውስጥ ወሳኝ የሚባሉትን መሰረታዊ መረጃዎች በማጠናከር አመራርን ዘመናዊ ለማድረግ የሚያግዙ ናቸው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ለአገር ውስጥ ገበያ የተዋወቁት የቴክኖሎጂ ውጤቶች በፍጥነት እያደገች ቻይና እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተተግብረው ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገቡ መሆናቸውን ዜድቲኢ ገልጾ፤ በአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አምራችነት ቀዳሚ ሥፍራ ለማግኘት አስችሎኛል ብሏል።

ስማርት ሲቲ የተሰኘው ቴክኖሎጂ የ 2013 የአለም አቀፍ የሞባይል ቴክኖሎጂ የሽልማት አሸናፊ እንደሆነ በቤጂንግ ከተማ ተተግብሮ የአለም አቀፍን የፈጠራ ተሸላሚ ለመሆን እንደበቃ ኩባንያው ገልጿል። ኢለርኒንግና ፓወር ግሪድ የተባሉት ቴክኖሎጂዎችም ከቻይና በተጨማሪ በሞሪሽየስ፣ በቬንዝዌላና በኬንያ ተሞክረው ውጤታማ መሆናቸው ጠነግሯል።

በፍጥነት እያደጉ ባሉት የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ውጤታማ እደሚሆኑ ዜድቲኢ ጠቅሶ፤ የኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት በ2020 ወደ 120 ሚሊየን ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅና ከዚህም ውስጥ 60 በመቶ ያህሉ በከተማ ይኖራል ተብሎ እንደሚገመት ተናግሯል።

Wednesday, 26 March 2014

“በስልክ የምናወራውን ሁሉ ያውቃሉ”




መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ‘ሂውማን ራይትስ ዎች’ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን እንደሚሰልል መጋቢት 16 ባወጣው ሪፖርቱ ገለፀ።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ 145 ገፅ በሚደርሰውና “THEY KNOW EVERYTHING WE DO: Telecom and InternetSurveillance in Ethiopia” የሚል ርእስ በሰጠው ሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግስት የቻይናና የአውሮፓ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በኢትዮጵያና በባህር ማዶ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዜጎችን የስልክና ኢንተርኔት እንቅስቃሴ እንደሚሰለል ገልጿል።

ስለ ሪፖርቱ ኤ.ኤፍ.ፒ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ሚንስተር አቶ ሬድዋን ሁሴን “የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለማጥፋት ከሚደረጉ ዘመቻዎች አንዱ መሆኑን ስለምናውቅ ለሪፖርቱ መልስ መስጠት አስፈለጊ አይደለም” በማለት ሪፖርቱን ቢያጣጥሉም ምንጮቻችን እንደገለፁት ከሆነ የመንግስት የስለላ ክንፍ የሆነው የመረጀና ደህንነት ኤጀንሲ INSA የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ በለቀቀው ሪፖርት ተደናግጠው ‘ውስጣችን መረጃ አሳልፎ የሚሰጥ አለ’ እስከማለት እንደደረሱ ምንጮቻችን ገልፀውልናል።

ሂውማን ራይትስ ዎች በርፖርቱ አያይዞ የደህንነቶች ሀይሎች የተቀዱ የስልክ ልውውጦችን በፈለጉት ጌዜ የሚያዳምጡ ሲሆን ካለምንም ህጋዊ ድጋፍ የዜጎችን ስልክ ጠልፎ በመቅዳት የተቃውሞ ድምፅን ለማፈን እንደሚጠቀሙበትና በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም የሚገኙ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚዎች ኮምፒተሮች ላይ ለስለላ የሚያገለግል ሶፍትዌር (spyware) በመላክ በኦንላይን የሚያደርጉትን እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን እንደሚሰልል ርፖርቱ ጠቅሷል።

በኢንተርናሽናል ኮምንኬሽን ዩንየን ጥናት መሰረት 23% ኢትዮጵያውያን የተንቀሳቀሽ ስልክ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ በስለላው ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያን መንግስት ትደግፋለች ተበላ የምትወቀሰው ቻይና

Saturday, 22 March 2014

HRW: #Ethiopia government Regularly Records Phone conversations

Washington Post

A rights group says that Ethiopia's government regularly
listens to and records the phone calls of opposition activists and journalists
using equipment provided by foreign technology companies.

Human Rights Watch said in a report Friday that the foreign equipment aids the
Ethiopian government's surveillance of perceived political opponents inside and
outside the country.

The group's Arvind Ganesan said Ethiopia is using its government-controlled
telecom system to silence dissenters. The group says that recorded phone calls
with family and friends are often played during abusive interrogations.

Human Rights Watch said most of the monitoring technology is provided by the
Chinese firm ZTE. Several European companies have also provided equipment,
the group said, including from the U.K., Germany and Italy.

Friday, 21 March 2014

INSA የማን ነው? የኢህአዴግ ወይስ የህዝብ?




ወደ ድረ ገጹ ስትገቡ ከፊት ለፊት የምታዩት የሚያስፈራ ሎጎ በሸረሪት ድር፣ በቁልፍና የቁልፍ ጋን ተደጋግፈው የሰሩት የተቋሙ መጠሪያ ሲታዩ እንደተቋሙ አላማ ደህንነትን ሳይሆን ስጋትን ይፈጥራሉ። (INSA) የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ። “Secured Cyber for Peace, Development and Democracy” የተቋሙ ሞቶ ነው።

የዚህ ተቋም ስልጣን አገሪቷን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ስነልቦናዊ ቀውስ ውስጥ ሊከቱ ይችላሉ ብለው የጠረጠሯቸው አካላት ላይ ካለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ድንገተኛ ምርመራና ብርበራ ያካሂዳል። ይህ ተቋም አደጋ ያመጣሉ ብሎ ያሰበውን ማንኛውም እንደ ኢንተርኔት ግንኙነት፣ ኮምፒውተሮች፣ የተለያዩ ኔትውርኮች፣ የሬድዮና የተሌቪዝን ስርጭቶች እና ማህበራዊ ድረገጾች ፌስቡክን ጨምሮ አስፈላጊውን ክትትልና ምርመራ እንዲያደርግባቸው ከተቃዋሚ ፓርቲ አንድ ተወካይ ብቻ ያለው የኢትዮጵያ ፓርላማ ሙሉ ስልጣን ሰጥቶታል።

የስለላ መሳሪያዎችን በብዙ ሚሊዮን ዶላሮች እየገዛ የሚያስገባው የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎችን የኢንተርኔት ግንኙነት መሰለል ብቻ ሳይሆን በብዙ ሚሊዮን ዶላሮች እየተገዙ በሚመጡ መሳሪያዎች የአጭር ሞገድ ሬዲዮ ጣብያዎችንና የሳተላይት ቴሌቭዝኖችን በማገድ ዜጎቻቸውን በስለላ ፋታ ከነሱት ኢራንና ቻይና ተርታ ተመድቧል።

“Secured Cyber for Peace, Development and Democracy”

ጋዜጠኖች፣ ተቃዋሚዎች እንዲሁም መንግስት ላይ ከፍተኛ ትችት የሚሰነዝሩ ግለሰቦች ያለጥርጥር በዚህ መስሪያ ቤት እይታ ውስጥ ናቸው። የተለያዩ ጥናቶችና ሪፖርቶች የሚያመለክቱትም የኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪዎችን